ዲናር የገንዘብ ቁጠባና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
ቁጠባን ባህል አድርጎ ከሌላ ወገን በሚገኝ የገንዘብ ምንጭ ሳይሆን በተቆጠበ የራስ ገንዘብ ህይወትን መቀየር፣ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎ የሚያምነው ዲናር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ኅ/ስራ ማህበር መደበኛና የፈቃድ ቁጠባ ለአባላቶቹ ያዘጋጀ ሲሆን አባላቶቹ ሼር በመግዛት አባል ከሆኑ በኃላ ቁጠባን ይጀምራሉ፡፡ ለከሶስት እስከ ስድስት ወር በተከታታይ በመቆጠብ የቁጠባ ባህላቸውን ካዳበሩ በኃላ ወደ ብድር እንዲሄዱ በማድረግ የራሳቸውን፣ የቤተሰባቸውን ብሎም የአገራቸውን እድገትና ለውጥ እንዲያፋጥኑ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የኅብረት ሥራ ማህበሩ መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ከ30 ቀናት (ከአንድ ወር) ገቢ ውስጥ 10 በመቶ ወይም ብር 500.00 (አምስት መቶ ) ነው
- እያንዳንዱ አባል ከመነሻ የቁጠባ መጠን በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ፣ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ እና የተለያዩ ቁጠባዎችን መቆጠብ ይችላል
- የፍላጎት ቁጠባ፡- መደበኛ መቆጠብ ካለበት 500 ብር ወይም ከገቢው 10 በመቶ በተጨማሪ የሚቆጠብ ቁጠባ ነው፡፡
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ፡-ኅብረት ስራ ማህበሩ እንደአስፈላጊነቱ ከአባላቱ ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሠረት ለተወሰነ ግዜ ለአስቀማጩ ተከፋይ የማይሆን የጊዜ ገደብ ቁጠባ ሊሰበስብ ይችላል
- ማንኛውም አመልካች አባል እንዲሆን ከተፈቀደለት ዕለት ጀምሮ ያለማቋረጥ በተከታታይ በየወሩ መደበኛ ቁጠባ መቆጠብ ይኖርበታል
- የትኛውም ቁጠባ አባልነት በሚቋረጥበት ወቅት ተመላሽ ይሆናል
- አባሉ የፍላጎት ቁጠባ ማውጣት ከፈለገ በፅሁፍ ወይም ኅብረት ሥራ ማህበሩ ባዘጋጀው ፎርም በመጠየቅ ማውጣት ይችላል። ሆኖም ተበዳሪ ወይም ዋስ ከሆነ ብድሩ ተከፍሎ ካላለቀ ወይም ዋስትናው ካልተነሳ ማውጣት አይቻልም
- አባሉ በፍላጎት ያስቀመጠውን የፍላጎት ቁጠባ፤ የተበደረው ብድር ቀሪ ዕዳው የፍላጎት ቁጠባውን ያህል ከሆነና ቁጠባው ለሌላ ተበዳሪ በዋስትና ካልተያዘ የፍላጎት ቁጠባውን ማጣጣት ይችላል፤ • አባሉ ያለውን መደበኛ ቁጠባ ማውጣት የሚችለው ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ነው።
ዲናዲናር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር ከአባላት መደበኛ እና የፍላጎት ቁጠባ ከአባላት ያሰባሰበውን ገንዘብ በኅብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ/በተወካይ አባላት በየጊዜው በሚሰጥ ውሳኔና በመተዳደርያ ደንብና በብድር መመሪያው በተቀመጠው መሠረት ለአባላት ብድር በመስጠት አባላት በፍላጎታቸው በሚመርጡዋቸው የተለያየ የሥራ መስክ በመሰማራት የገቢ ምንጫቸውን እንዲያሰፉና ኑሮአቸው እንዲሻሻል በማድረግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል:: በመሆኑም ለአባላቱ የመደበኛ
Brochures
Our brokerage services include buying and selling mutual funds, stocks, bonds and other types of individual securities in our Full Service or Self Directed brokerage account types. More investment products are available in a Full Service account compared to a Self Directed account


